የሸማቾች አሥርቱ ትዕዛዛት
የሸማቾች አሥርቱ ትዕዛዛት
- የምትገዟቸውን ቁሳቁሶች ከወዲሁ አስቀድሞ ማቀድ ያስፈልጋል ።
- አንድን ቁሳቁስ ወይም አገልግሎት ከመግዛትህ በፊት ወደ ሌላ የመገበያያ ቦታዎች በመሄድ ዋጋውን አነፃጽሩ ።
- ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቁሳቁሶችን ዋጋ በሚያሳይ ድርጅት መግዛታችሁን አረጋግጡ ።
- የአምራቹ ስም ፤ አድራሻውና የዋስትና ምስክር ወረቀት ያለበት ምርት መግዛታችሁን አረጋግጣችሁ ግዙ ።
- የምትገዙት ቁሳቁሶች ለደህንነት እና ለጥራት ዋስትና የሚሰጥ ምልክት ያለበትን ምርት አይታችሁ ግዙ ።
- ከመፈረማችሁ በፊት እያንዳንዱን ስምምነት ተቀብላችሁ በጥሞና አንብብቡት ።
- የገዛችሁት ቁሳቁስ በእጃችሁ ከገባ በኋላ እንጅ ቀድማችሁ ክፍያ አትፈጽሙ ፤ ለከፈላችሁት ሙሉ ገንዘብ ደረሰኝ ተቀበሉ ።
- በመንገድ ላይ ወይም ወደ _ ቤታችሁ እየመጡ ሊሸጡላችሁ ከሚፈልጉ ግለሰቦች የዘፈቀደ ግብይት ተቆጠቡ ።
- የገንዘብ መክፈያ የካርድ ዝርዝሮችን በስልክ መስመር ወይም በኢንተርኔት ለማይታወቁ አካላት ከመስጠት ተቆጠቡ ። በማንኛውም ጊዜ በኡንተርኔት የሚደረጉ ግብይቶች ደህንነቱ በተጠበቀ የኢንተርኔት መስመር ላይ መደረጉን አረጋግጡ ።
- ከባንኮቻችሁ የምትቀበሏቸውን ቸኮች በሁለት መስመሮች ("ሰረዞች") ምልክት የተደረገባቸው መሆኑን ማረጋገጥና "ለተጠቃሚው ብቻ" (የተከፈለው ለ… ነው የሚል መጻፍ የለበትም) አገልግሎት ላይ የሚውል መሆኑ አረጋግጡ ፤ በቼኩ ላይ ስሙን እና የገንዘቡን መጠን በእጅ ጽሑፍ ብቻ መሙላይ ያስፈልጋል ።

በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።
































