የግዢ ማስታወሻዎች
ሕጉ የግዢ ትዕዛዞችን በተመለከተ ልዩ ድንጋጌዎችን ያዘጋጃል፣ ከታች ያሉት ዝርዝሮች ዋናዎቹ ናቸው ፤
የግዢ ትዕዛዝ ትክክለኛነት
- እያንዳንዱ የመግዣ ትዕዛዝ ቢያንስ ቢያንስ ለአምስት ዓመታት ያገለግላል ።
- የመግዣ ትዕዛዙን የሚሰጠው አካል የሚያልቅበትን ቀን ለመለወጥ ከፈለገ ፤ ይህን ማድረግ የሚችለው የመግዣው ትዕዛዝ አምስት ዓመት ካለፈው በኋላና ፈቃዱን የሚሰጠው አካል ስምና የወጣበት ቀን ጎላ ብሎ በዝርዝር ከተጻፈ ብቻ ነው ።
- በተጨማሪም ፤ ይህ የመግዣ ትዕዛዝ በማንኛውም የገብያ ቦታ ዋጋው 95% ወይም 90% ብቻ መከበር ያስፈልገዋል ብሎ መወሰን አይቻልም ፤ ማንኛውም የገብያ ቦታ ይህን የመግዣ ፈቃድ 100% ተግባር ላይ ማዋል አለባቸው ።
በመግዣ ትዕዛዝ ገዝተን መልስ ቢኖረን
አንድ ሸማች ለግዢ ከልክ ያለፈ ክፍያ ሲቀበል ፤ ሻጩ ተመልሶ የሚገዛበት የደረሰኝ ፈቃድ መስጠት እንጂ ጥሬ ገንዘብ ሊሰጠው አይችልም ፤ ጥሬ ገንዘብ መስጠት የሚችለው እነዚህ የመግዣ ትዕዛዝ ፈቃዶች ያላቸው የንግድ ምልክት አንድ ዓይነት ከሆነ ብቻ ይሆናል ።

በመግዣ ትዕዛዝ በመጠቀም የተገዛውን ምርት ስለመመለስ
የመግዣ ትዕዛዝ ፈቃድን ተጠቅሞ የተገዛ ምርት ከተመለሰ ፣ሻጩ በጥሬ ገንዘብ ከመመለስ ይልቅ ተመልሶ የመግዣ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል ፤ ይህ የሚሆነውም በመግዣ ትዕዛዝ አጠቃቀም ላይ ምንም ገደብ ከሌለ ብቻ ነው ፤ (በዚህ የመጠቀሚያ ካርድ ላይ ቀደም ሲል የነበረ ገደብ ካልሆነ በስተቀር) ።
የገንዘብ ማስመለሻ ካርድ ወይም ስጦታ
አንዳንድ ጊዜ ሻጩ ለሸማቹ የገዛውን ዕቃ የመመለስ መብት ያለው፣ ሁኔታዎች ካልተሟሉ የሸጨውን ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ለመግዛት የተስማሙበትን ስምምነት ለመሰረዝ ይችላል ። አብዛኛውን ጊዜ ፤ እንደዚህ ባሉ አጋጣሚዎች ሻጩ ለተጠቃሚው የብድር መመለሻ ካርድ ይሰጣል ። ሕጉ በብድር መመለሻውና በስጦታው ካርድ ላይ የተጻፈው እንዳይሰረዝ በሚያግድ መንገድ መታተም ወይም መጻፍ አለበት ይላል ። በብድር መመለሻው ውስጥ የተገለው የገንዘብ መጠን በግብይቱ ወቅት የሚከፈለው መጠን ይሆናል ፤ የብድር መመለሻው ካርድ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለሁለት ዓመታት ያገለግላል ፤ የመግዣውን ካርድ በመጠቀም የክፍያ መጠየቂያ ደረሰኝ ጊዜ የተወሰነ አይሆንም ። በልዩ ሽያጭ ውስጥ የመግዣ ካርዶችን ጨምሮ ማንኛውንም ካርድ የማስመለስ ዕድልን የሚገድቡ ሁኔታዎች ተቀባይነት የላቸውም ።
ሕጉ በእነዚህ ክርዶች ላይ ገደቦችን የሚፈቅዱ ደንቦችን ጨምሮ እንዲያስገባ ይፈቅዳል ፤ ነገር ግን ይህ መመሪያ ከተጠናቀረበት ጊዜ ጀምሮ እንደዚህ ያሉ ደንቦች ገና ከካርዱ ውስጥ አልገቡም ነበር ።
በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።
































