የሸማቾች አሥርቱ ትዕዛዛት

የሸማቾች አሥርቱ ትዕዛዛት

  1. የምትገዟቸውን ቁሳቁሶች ከወዲሁ አስቀድሞ ማቀድ ያስፈልጋል ።
  2. አንድን ቁሳቁስ ወይም አገልግሎት ከመግዛትህ በፊት ወደ ሌላ የመገበያያ ቦታዎች በመሄድ ዋጋውን አነፃጽሩ ።
  3. ሕጋዊ በሆነ መንገድ የቁሳቁሶችን ዋጋ በሚያሳይ ድርጅት መግዛታችሁን አረጋግጡ ።
  4. የአምራቹ ስም ፤ አድራሻውና የዋስትና ምስክር ወረቀት ያለበት ምርት መግዛታችሁን አረጋግጣችሁ ግዙ ።
  5. የምትገዙት ቁሳቁሶች ለደህንነት እና ለጥራት ዋስትና የሚሰጥ ምልክት ያለበትን ምርት አይታችሁ ግዙ ።
  6. ከመፈረማችሁ በፊት እያንዳንዱን ስምምነት ተቀብላችሁ በጥሞና አንብብቡት ።
  7. የገዛችሁት ቁሳቁስ በእጃችሁ ከገባ በኋላ እንጅ ቀድማችሁ ክፍያ አትፈጽሙ ፤ ለከፈላችሁት ሙሉ ገንዘብ ደረሰኝ ተቀበሉ ።
  8. በመንገድ ላይ ወይም ወደ _ ቤታችሁ እየመጡ ሊሸጡላችሁ ከሚፈልጉ ግለሰቦች የዘፈቀደ ግብይት ተቆጠቡ ።
  9. የገንዘብ መክፈያ የካርድ ዝርዝሮችን በስልክ መስመር ወይም በኢንተርኔት ለማይታወቁ አካላት ከመስጠት ተቆጠቡ ። በማንኛውም ጊዜ በኡንተርኔት የሚደረጉ ግብይቶች ደህንነቱ በተጠበቀ የኢንተርኔት መስመር ላይ መደረጉን አረጋግጡ ።
  10. ከባንኮቻችሁ የምትቀበሏቸውን ቸኮች በሁለት መስመሮች ("ሰረዞች") ምልክት የተደረገባቸው መሆኑን ማረጋገጥና "ለተጠቃሚው ብቻ" (የተከፈለው ለ… ነው የሚል መጻፍ የለበትም) አገልግሎት ላይ የሚውል መሆኑ አረጋግጡ ፤ በቼኩ ላይ ስሙን እና የገንዘቡን መጠን በእጅ ጽሑፍ ብቻ መሙላይ ያስፈልጋል ።

በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።