በአንድ ወገን ብቻ የተዘጋጁ ስምምነቶች

በአንድ ወገን ብቻ የተዘጋጁ ስምምነቶች

በአንድ ጎን ብቻ የተዘጋጁ ዉሎች ማለት “ቁጥራቸው ባልታወቀ ሰዎች ወይም በማንነታቸው በማይታወቁ ሰዎች መካከል ለሚደረጉት ብዙ ውሎች ፣ በአንድ ተዋዋይ ወገን ውሉ በሙሉ ወይም በከፊል የተወሰነው የውል ሰነድ ነው " ይህ ሻጭ ለሸማቹ ውል የሚያቀርብበት ሁኔታ አስቀድሞ በሻጩ በተወሰነው ስምምነት ዓይነት (ይህ ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚውልበት ሁኔታ ለምሳሌ በግንኙነቶች መስክ ከትላልቅ ኩባንያዎች ጋር ውል ሲደረግ ፤ የባንክ አገልግሎት፣ የኋይል አቅርቦት) ጉልበት የሚሰጠው ሰነድ ማለት ነው ። የዚህ ዓይነት ውልን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች የተመሰረቱት በአንድ ጎን ብቻ የተዘጋጁ ዉሎችን በሚመለከተው ሕግ መሰረት ነው። ሕጉም የተደነገገው በ 1982 ዓ.ም ሲሆን፣ ዓላማው ሸማቾችን ከአደጋ ከሚያስከትሉ ሁኔታዎች ለመጠበቅ ነው። ይህም ሲባል በፓርቲዎች መካከል ባለው የመረጃና የስልጣን ክፍተት ምክንያት የሸማቹ ህብረተሰብ ለችግር መዳረጉን በመረዳት ነው ።

መድሏዊ ድርጊቶች ማለት ፤ ሸማቾችን የሚጎዳ ወይም ለነጋዴው የኢ-ፍትሃዊ ጥቅም የሚያደላና ሸማች የሚደርሱትን ጥቅሞች እንዲያጣ የሚያደርግ ሁኔታ ነው ።

ከዚህ በታች በሕግ የተደነገጉ ሁኔታዎች መድሎ ናቸው ተብሎ የሚታመኑ አንዳንድ ምሳሌዎችን ያቀርባሉ ።

  1. አገልግሎት አቅራቢውን በሕግ ከተጣለበት ተጠያቂነት፣ነፃ የሚያደርገው፣ ወይም ያለምክንያት በስምምነቱ መሰረት የጣልበትን ኋላፊነት ላለመወጣት የሚያደርገው ሁኔታ ።
  2. የሻጩ ሁኔታ የውሉን አፈጻጸም ለመሰረዝ፣ ለማገድ ወይም ለሌላ ጊዜ ለማስተላለፍ ወይም በውሉ መሰረት አስፈላጊ የሆኑትን ድርጊቶች የመቀየር ሕጋዊ ያልሆነ መብትን ለሻጩ የሚሰጠው ።
  3. ሻጩ ኃላፊነቱን ለሶስተኛ ወገን የማስተላልፍ መብት የሚሰጥበት ሁኔታ ።
  4. ውሉ ከተጠናቀቀ በኋላ አቅራቢው በደንበኛው ላይ የሚጣለውን ዋጋ ወይም ሌላ ጉልህ ክሶች የመወሰን ወይም የመቀየር መብት የሚሰጠው ሁኔታ (ከአቅራቢው ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ሁኔታዎች ምክንያት ለውጥ ካልሆነ በስተቀር) ።
  5. በውሉ መሠረት የአንድን ዋጋ ወይም ሌላ ክፍያ ከአንዳንድ ማመዛዘኛ ንግዶች ጋር ማገናኘት የሚወስንበት ሁኔታ ፤ ስለዚህም የማመዛዘኛ ንግዶች መቀነስ ወይም መጨመር ለደንበኛው አይጠቅምም ።

ፍርድ ቤቱና የፍርድ መስጫ ተቋሞች ለሚደረጉ ዉሎች፣ ልዩና በአንድ ወጥ ውል ውስጥ ያሉ መጥፎ ሁኔታዎችን ለመሰረዝ ወይም ጉዳት እንዳይደርስባቸው እንዲቀይሩ ተፈቅዶላቸዋል ።

በዚህ የመምሪያ መጽሔት ውስጥ የቀረበው መረጃ አጠቃላይ መረጃ ብቻ ነው ፤ ግን ሕጋዊ ምክርን የሚተካ አይደለም እና ያለ ተገቢ ምክር ብቻዉን መታመን የለበትም.
ይህ መምሪያ ሰኔ ወር 2023 ዓ.ም. ያለውን መረጃ በሕጉ እና ደንቡ ላይ በመመርኮዝ ተሻሽሏል ።
አስገዳጅ የሚሆነው የሕጉ እና የደንቡ ጽሑፍ ነው።